loading
በልዩ ልዩ ሸቀጣ ሸቀጦች እና የፅዳት ዕቃዎች ላይ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉት ግለሰቦች ላይ ምርመራ እያጠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 9፣ 2012 በልዩ ልዩ ሸቀጣ ሸቀጦች እና የፅዳት ዕቃዎች ላይ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ባደረጉት ግለሰቦች ላይ ምርመራ እያጠራ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ፡፡

ህገ-ወጦች ላይ እየተደረገ ያለው ቁጥጥር ተጠናክሮ መቀጠሉን ኮሚሽኑ አስታወቋል፡፡
በአዲስ አበባ የኮረና ቫይረሰ መከሰቱን ምክንያት በማድረግ አንዳንድ ግለሰቦችና የንግድ ተቋማት በፊት መሸፈኛ ማስክ ፣ በፅዳት ዕቃዎች እና በልዩ ልዩ ሸቀጣ ሸቀጦች ላይ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ማድረጋቸውን ተከትሎ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር ባደረገው ክትትል ህገ-ወጦችን ይዞ ምርመራውን እያጣራ መሆኑን አስታውቋል፡፡
በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን መድሃኒት እንረጫለን በሚል ምክንያት የዘረፋ ወንጀል እንደተፈፀመ ተደርጎ የተሳሳተ መረጃ እየተላለፈ መሆኑን ኮሚሽኑ አስታውሶ በሚዲያዎች የተላለፈውን መረጃ በተመለከተ ምንም አይነት ጥቆማ እንዳልደረሰውና የተመዘገበ ወንጀል አለመኖሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል፡፡
ህብረተሰቡ በቫይረሱ እንዳይያዝ እና ወንጀል እንዳይፈፀምበት እያደረገ ያለውን ጥንቃቄ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

በሸቀጣ ሸቀጦች ሆነ በንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ላይ ተገቢ ያልሆነ ጭማሪ ያደረጉ እና እጥረት እንዲፈጠር የሚሸሽጉ አካላት ሲያጋጥሙት ጥቆማ ለመስጠት እንዲሁም ከወንጀል ጋር ተያይዞ የፖሊስን አገልግሎት ሲፈልጉ በየአካባቢው ካሉ ስልኮች በተጨማሪ 991 ወይም 816 ነፃ የስልክ መስመሮችን እና 01- 11 -11- 01 -11/ 01- 11- 26- 43- 59 እና በ01- 11- 01- 02- 97፣ መጠቀም የሚችል መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *