በልደታ ክ/ከተማ በህገወጥ መንገድ ተይዘው የነበሩ 250 የቀበሌ ቤቶች ለችግረኛች ተሰጡ።
አርትስ 29/01/2011
በህገወጥ መንገድ ተይዘዉ የነበሩት ቤቶች ምክትል ከንቲባ ኢንጅነር ታከለ ኡማ በተገኙበት የቁልፍ ርክክብ ተደርጓል።
በህገወጥ መንገድ ተይዘው የቆዩ ቤቶችን በመለየት በቤት እጦት ለሚንገላታው ነዋሪ የማስተላልፍ ስራ በሁሉም ክፍለከተሞች ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኢንጅነር ታከለ ተናግረዋል።
በተመሳሳይ ቂርቆስ ክፍለከተማም 199 ቤቶች ተለይተው ለችግረኞች መተላለፋቸው ይታወሳል።