በመላዉ ዓለም የኮቪድ 19 ክትባት መሰጠት መጀመሩ ኢትዮጵያን ከቫይረሱ እንዳይጠነቀቁ ሊያደርግ አይገባም::
አዲስ አበባ፣ጥር 03፣ 2013 በመላዉ ዓለም የኮቪድ 19 ክትባት መሰጠት መጀመሩ ኢትዮጵያን ከቫይረሱ እንዳይጠነቀቁ ሊያደርግ አይገባም ሲሉ አርትስ ያነጋገራቸዉ በሚሊኒየም የኮቪድ 19 ኬር ሴንተር የነርስኒግ ዳይሬክተር ሲስተር ንጋት ወ/ማርያም አሳሰቡ ፡፡ በማዕከሉ ቀደም ሲል ከነበረዉ የታማሚዎች ቁጥርና የፅኑ ህክምና የሚያስፈልጋቸዉ ሰዎች ቁጥር መበራከታቸዉን ያስታወሱት ሲስተር ንጋት ፤የኮቪድ 19 ክትባት ቢገኝም ለአፍሪካ ብሎም ለኢትዮጵያ
ተዳራሽ የመሆኑ ጉዳይ ከአቅም ጋር በተያያዘ ጊዜ እንደሚወስድ በመግለፅ ህብረተሰቡን ቀደም ሲል ሲያደርግ ከነበረዉ ጥንቃቄ ሊያዘናጋዉ እንደማይገባ አሳስበዋል ፡፡