በመቄዶኒያ ለሚገኙ አረጋዊያን ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና እየተሰጠ ነው
በመቄዶኒያ ለሚገኙ አረጋዊያን ነጻ የዓይን ሞራ ግርዶሽ ህክምና እየተሰጠ ነው
አርትስ 12/03/2011
አገልግሎቱን የሚሰጠው አልባሳር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ያሲን ራጁ ለአርትስ እንደተናገሩት ድርጅቱ 16 የአይን ሀኪሞች፣ መነጽሮችን ፣ መድሃኒቶችንና ሌሎች አስፈላጊ የህክምና ግብአቶችን ዝግጁ በማድረግ በአለርት ሆስፒታል እየሰጠ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
ባለፉት ሁለት ቀናት 4ሺህ የሚሆኑ አዲስ አበባ ነዋሪዎች አገልግሎቱን አግኝተዋል። በቀጣይ ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ቀጠሮ መሰጠቱንና እስከ አርብ ለሚመጡ ዜጎች አገልግሎቱን ለመስጠት ዝግጁ መሆኑን ነግረውናል፡፡
በዛሬ ውሎዋቸውም በመቄዶኒያ የአረጋዊያን መርጃ ማዕከል 400 ለሚሆኑ አረጋዊያን አገልግሎቱ እንደሚሰጥ አቶ ሲራጅ ነግረውናል፡፡
የአይን ጤና ችግር ያለባቸውን ህሙማን የመመርመር፣ የሞራ ችግር ያለበናቸውን የቀዶ ጥገና አገልግሎት የመስጠት እና ሌሎች የአይን ችግር የተገኘባቸውን የማማከር፣የመድሃኒት እና የመነጽር ድጋፍ እንደሚደረግም ተናግረዋል፡፡ መስፈርቱም መክፈል የማይችሉ ማንኛውም የአዲስ አበባ ነዋሪ መሆን ብቻ በቂ እንደሆነም አስታውሰዋል፡፡