loading
በመዲናዋ በ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር 100 ሺህ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 በመዲናዋ በ4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር 100 ሺህ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ:: በአዲስ አበባ ከተማ በአንድ አመት ውስጥ 100 ሺህ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡ ስምምነቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ፕሮፐርቲ 2000 ደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ተወካይ ተፈራርመውታል፡፡ ለግንባታው 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ወጪ የሚደረግ ሲሆን፥ ሙሉ ወጪው በኩባንያው ይሸፈናል ተብሏል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ለግንባታ የሚያስፈልገውን መሬት ያቀርባል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *