loading
በመዲናዋ “አንድ መምህር ለአንድ ቤተሰብ” በሚል የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጀመረ::

አዲስ አበባ፣ሐምሌ14፣ 2012 በመዲናዋ “አንድ መምህር ለአንድ ቤተሰብ” በሚል የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተጀመረ::የአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ ከወጣቶች እና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ እንዲሁም የግል ትምህርት ቤቶች ማህበር ጋር በመተባበር ነው መርሃ ግብሩን የጀመረው። ይፋ በተደረገው የክረምት ማጠናከሪያ ትምህርት የበጎ ፍቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር ላይ የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ የሰራ ኃላፊዎች፣ የከተማው መምሀራን ማህበር አባላት፣ የአዲስ አበባ የወጣቶችና የበጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ፣ የግል ትምህርት ቤቶች ማህበርና መምህራን ተገኝተዋል። የክረምት በጎ ፍቃድ ማጠናከሪያ ትምህርት ፕሮግራሙ በኮቪድ-19 ወረርሽን ሳቢያ የተቋረጠውን የትምህርት ክፍለ ጊዜ ለማካካስ እና ተማሪዎች ለ2013 የትምህርት ዘመን ከወዲሁ ዝግጁ እንዲሆኑ ያግዛል ተብሏል። በዚህ የማጠናከሪያ ትምህርት መርሃግብር ከመምህራን በተጨማሪ ከተለያዩ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ተሳታፊ መሆናቸው ተገልጿል። በአሁኑ ጊዜ መምህራን በተለያዩ የበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ላይ መሆናቸዉ የተገለጸ ሲሆን  በዚህ ስራ ላይ የአንበሳዉን ድርሻ እንደሚወስዱም የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ መረጃ ያመለክታል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *