በማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎች በአሁኑ ወቅት ፈተና መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ተናገሩ፡፡
በማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎች በአሁኑ ወቅት ፈተና መሆናቸውን ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ተናገሩ፡፡
ፕሬዝዳንቷ ይህንን የተናገሩት የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን በኢትዮጵያ እየተከበረ ባለበት ወቅት ነዉ፡፡
ከረቡዕ ጀምሮ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች መከበር የጀመረው 26ኛውን አለም አቀፍ የፕሬስ ነፃነት ቀን፥ በዛሬው እለትም በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ በሚካሄድ ውይይት ቀጥሎ ውሏል።
በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ ባለው መርሃ ግብር ላይም መገናኛ ብዙሃን በነፃና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲሁም በዴሞክራሲያ ስርዓት ግንባታ ላይ ባላቸው ሚና ላይ ትኩረት በማድረግ ነው እየመከረ ነዉ፡፡
በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ እየተካሄደ ባለው የዓለም ፕሬስ ነፃነት ቀን ላይም የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ ባደረጉት ንግግርም በኢትዮጵያ ከፍተኛ ለውጥ እየተካሄደ መሆኑን በመጥቀስ፤ ለውጡም ለሚዲያው ነፃነት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልፀዋል።
ኢትዮጵያም በቀጣይ ዓመት ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት ላይ መሆንዋንም ተናግረዋል፡፡
በማህበራዊ ትስስር ድረ ገፅ የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎች በአሁኑ ወቅት ፈተና መሆናቸውን ያነሱት ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ፤ የዓለም የፕሬስ ነፃነት ቀን ተሳታፊዎች በማህበራዊ ትስስር ድረ ገፆች የሚለቀቁ የሀሰት መረጃዎችን እንዴት መከላከል ይቻላል የሚለው ላይ ትኩረት አደርገው እንዲመክሩ እና እንዲሰሩም ጠይቀዋል።