በማዳስካሩ ምርጫ የአሁኑና የቀድሞዎቹ ፕሬዝዳንቶች አንገት ለአንገት ተናንቀዋል
አርትስ 29/02/2011
በአሁኑ የማዳስካር ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ሀገሪቱን የሚመሩት ሄሪ ራጆናሪማም ፒያኒ እንዲሁም ሁለቱ የቀድሞ ፕሬዚዳንቶች አንድሪ ራጆሊና እና ማርክ ራቫሎ ማናና ለድሉ ተፋጥጠውበታል፡፡
በአንድ ወቅት ማዳስካርን ሲያስተዳድሩ የነበሩት ማርክ ራቫሎ ማናና ገና በቆጠራ ላይ ስላለው የምርጫ ውጤት ከፊቴ ጥሩ ተስፋ ይታየኛል፤ በእርግጠኝነት ዳግም ምርጫ አይኖርም ብለዋል፡፡
ኒውስ አፍሪካ እንደዘገበው ምርጫውን የታዘበው የአውሮፓ ህብረት እስካሁን ባለው ሂደት ምንም ዓይነት የተዛባ ለገር ባለማየቴ ደስተኛ ነኝ ብሏል፡፡
ሌላው እጩ ተፎካካሪ ሆነው የቀረቡት የቀድሞው ፕሬዝዳንት አንድሪ ራጆሊና በበኩላቸው ውጤቱ ይፋ ከመሆኑ በፊት ያሉ ነገሮች ተስፋ ሰጭ በመሆናቸው ረክቻለሁ ነው ያሉት፡፡
የወቅቱ ፕሬዝዳንት ደግሞ የዛሬው ቀን ታላቅ ነው፤ ምክንያቱም ምርጫው በዚህ መልኩ መካሄዱ ዴሞክራሲያዊ ድል ነው በማለት የድምፅ አሰጣጡ ሄደት በሰላም መጠናቀቁን አድንቀዋል፡