loading
በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ለህዳሴ ግድብ ግንባታ ከቦንድ ሽያጭ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ ለማሰባሰብ እየተሰራ ነው ተባለ::

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 13 ፣ 2013 በምስራቅ ሐረርጌ ዞን ለታላቁ የኢትዮዽያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ10 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ የማሰባሰብ ስራ እየተካሄደ መሆኑን የዞኑ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ማስተባበርያ ምክር ቤት አስታዉቋል::የታላቁ የኢትዮዽያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ 10ኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የቦንድ ግዢ ሳምንት በዞኑ አወዳይ ከተማ በይፋ ተጀምሯል::

የዞኑ የታላቁ የህዳሴግድብ ግንባታ ማስተባበርያ ምክር ቤት ፀሃፊ አቶ መሀመድ በወቅቱ እንደተናገሩት በኢትዮጵያውያን ብቻ በመገንባት ላይ የሚገኘው የህዳሴ ግድብ ግንባታ ስራ ለአፍታ ሳይቋረጥ በተጠናከረ መልኩ እንዲጓዝ የዞኑ ህዝብ የራሱን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል።የህዳሴ ግድብ መሰረት ከተጣለበት ቀን ጀምሮ በዞኑ ከሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች፣ ለሀብቶ፣ አነስተኛና ጥቃቅን ማህበራት፣ ከአርሶ አደርና ከሌሎች የህብረተሰብ ክፍል በቦንድ
ሽያጭና በስጦታ ከ130 ሚሊየን ብር በላይ ተሰብስቦ ገቢ መደረጉን ተናግረዋል።

የዞኑ ብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ሃላፊ ወይዘሮ ሰዓዳ አብዱረሃማን  ህብረተሰቡ የኔ ነው ብሎ ለሚያምነ ውና ተስፋ ለሰነቀበት የህዳሴ ግድብ ግንባታ ስኬታማነት አመራሩ በቁርጠኝነት እንደሚሰራ ገልጸዋል::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *