በምዕራብ ጉጂ ዞን የጥምቀት በዓል በሰላም መከበሩ ተገለፀ ::
አዲስ አበባ፣ጥር 12፣ 2013 በምዕራብ ጉጂ ዞን የጥምቀት በዓል በሰላም መከበሩ ተገለፀ :: የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ለአርትስ በላከዉ መግለጫ በዞኑ በሁሉም ወረዳዎች የከተራና የጥምቀት በዓል በሠላም ተከብሯል ፡፡ በዓሉን በ ገላና ወረዳ ከቶሬ ከተማ የከበሩ ነዋሪች በሰጡት አሰተያየት የዘንድሮ የጥምቀት
በዓል ልዩ ነው የሌላ እምንት ተከታዮች ለበአሉ ድምቀት ያደረጉት በጎ ተግባር ፍቅራችን ይበልጡን እንዲዳብር አድርጎታል ብለዋል፡፡
በሌላ በኩል ይህ የጥምቀት በዓል በዩኒሰኮ የተመዘገበ የሁሉም ህዝብ ሀብት በመሆኑ ኩራት ይሰማናል ብለዋል፡፡ ከመቼውም ጊዜ በላይ አንድነታችንን በማጠናክር ሀገራችንን ለማፍረሰ እየሰሩ ያሉትን ሀይሎችን ለማጋለጥ መሰራት ይኖረብናል ብለዋል አሰተያየት ሰጪዎቹ፡፡ በገላና ወረዳ የቶሬ ደብር ፀሐይ ቅዱሰ ጊዮርጊሰ ድብር ዋና ሰራ አሰካጅ መላከለፀሐይ ተሰፍዬ በዓሉን አሰመልክቶ ባስተላለፉት መልዕክት፤ በአንድንት በመከባበር መኖር ከሁላችንም ይጠበቃል ብለዋል፡፡ ዕለቱን የሚዘክሩ ዝማሬዎችንና ትምህረቶችን በመሰጠት በዓሉ በሠላም ተከብሮ መዋሉን ኮሚኒኬሸን በላከልን መረጃ አስታዉ አስታዉቋል፡፡