loading
በሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ የሚካሄደው የዘር ማጥፋት ጥቃት ቀጥሏል

አርትስ 15/02/2011

ጥቃቱን ተከትሎ 700 ሺህ ሰዎች ከመኖሪያቸው ሲፈናቀሉ በርካቶች መገደላቸውን እና መደፈራቸውን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ገልጿል፡፡

በማይናማር የሮሂንጊያ ሙስሊሞች ላይ የሚፈፀመው የዘር ማጥፋት ጥቃት መቀጠሉንና የሀገሪቱ መንግስት ዲሞክራሲያዊ ስርዓትን ለመዘርጋት  እየሰራ አይደለም ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኮንኗል።

አልጀዚራ እንዳስነበበው በማይናማር የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የእውነት አፈላላጊ ልዑካን ሀላፊ ማርዙቂ ዳሩስማን፥ ከ250 ሺህ እስከ 400 ሺህ የሚገመቱ በሃገሪቱ የሚኖሩ የሮሂንጊያ ሙስሊሞች ባለፈው ዓመት ሲደርስባቸው የነበረው ጥቃት  በአሁንም  እንደቀጠለ ነው ብለዋል።

የዘር ማጥፋት ጥቃቱ መቀጠሉን ተከትሎም ማይናማር እርምጃ እንድትወስድ በአለም አቀፉ ህብረተሰብ እየተጠየቀች ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *