loading
በሰሜን ምእራብ ናይጀሪያ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 23 ወታደሮች ተገደሉ፡፡

አዲስ አበባ፣ሐምሌ13፣ 2012 በሰሜን ምእራብ ናይጀሪያ ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት 23 ወታደሮች ተገደሉ፡፡ ታጣቂዎቹ በካትሲና ግዛት ጂቢያ በተባለው አካባቢ በአንድ ጫካ በሚዘዋወሩበት ወቅት ወታደሮቹላይ ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት ነው ጉዳቱን ያደረሱት፡፡ አልጀዚራ እንድዘገበው ከሞቱት በተጨማሪ ከጥቃቱ በኋላ የገቡበት ያልታወቀ የሰራዊቱ አባላት መኖራቸው ተረጋግጧል፡፡ ከአሁን ቀደም በአካባቢው ያልታወቁ ታጣቂዎች ከብቶችን ዘርፈው እና ሰዎችን አግተው ሲሰወሩ ከቦኩሃራም ጋር ግንኙነት ያላቸው ሀይሎች ሊሆኑ ይችላሉ የሚል ስጋት ተፈጥሮ ነበር፡፡ ቀደም ሲል ስጋታቸውን የገለፁት የአካባቢው ባለስልጣናት ሁኔታው ከግምታቸው ሩቅ እንዳልሆነም ተናግረዋል፡፡ የናይጀሪያ ጦር ሀይል የስጋት ምንጮች ናቸው በተባሉ አካባቢዎች መደበኛ የቅኝት ስራችዎን ቢያከናውንም እስካሁን ዜጎቹን ከቦኩሃራም ጥቃት በአግባቡ መከላከል አለመቻሉ ይነገራል፡፡ መቀመጫውን ብራሰልስ ያደረገ ክራይስስ ግሩፕ የተባለ ተቋም ባወጣው ሪፖርት በናይጀሪያ የተሰማራው እስላማዊ ታጣቂ ቡድን እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2011 ጀምሮ ከ8 ሺህ በላይ ሰዎችን ሲገድል ከ200 ሺህ በላይ ዜጎች መኖሪያ ቀያቸውን ጥለው እንዲፈናቀሉ አድርጓል ብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *