loading
በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ጂሃዲስቶች ባደረሱት ጥቃት 13 ወታሮች ተገደሉ::

አዲስ አበባ፣ጥር 04፣ 2013 በሰሜን ምዕራብ ናይጄሪያ ጂሃዲስቶች ባደረሱት ጥቃት 13 ወታሮች ተገደሉ:: በዮቤ ግዛት በምትገኝ አንዲት መንደር አቅርቢያ በሚጓዙ ወታደራዊ ተሸከርካሪዎች ላይ በድንገት በተከፈተ ጥቃት ነው ወታደሮቹ የተገደሉት ተብሏል፡፡ አፍሪካ ኒውስ ወታደራዊ ምንጮችን ጠቅሶ እንደዘገበው የደፈጣ ተዋጊዎቹ በከባድ መሳሪያዎችና በሮኬት በሚወነጨፉ የእጅ ቦንቦች ጭምር ነው ጥቃቱን ያደረሱት፡፡

ወታደሮቹ ጥቃቱ ከተፈፀመበት 20 ኪሎሜትር ርቀት ላይ ወደሚገኘው የጦር ካምፕ በመጓዝ ላይ እንዳሉ ነው ድንገተኛ ተኩስ የተከፈተባቸው፡፡
የናይጄሪያ ወታደራዊ አዛዦች በሰጡት መግለጫ ከጂሃዲስቶቹ ጋር ያረጉት ውጊያ ከባድ እንደነበር አስታውሰው በርካታ ታጣቂዎችን መግደላቸውንም ተናግረዋል፡፡

ከመንግስት ወታደሮች ተገድለዋል የተባሉትን በተመለከተ ግን በወታደራዊ መኮንኖችና በበላይ ሃላፊዎች መግለጫ የቁጥር ልዩነት እንዳለ ዘገባው አመልከክቷል፡፡ ቦኩ ሀራም የተባለው የምእራባዊያንን ባህል አጥብቆ የሚቃወመው ቡድን ናይጀጄሪያን ላለፉት 10 ዓመታት እንዳትረጋጋ በማድረግ ከ36 ሺህ በላይ ዜጎችን መግደሉ ይታወሳል፡፡ ይሄ ቡድን የሚያራምደው የሽብር እንቅስቃሴ ከናይጄሪያ አልፎ ጎረቤት ቻድ፣ ኒጄርና ካሜሮን በመዛመት ቀጠናው እንዳይረጋጋ ዳርጎታል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *