በሰራተኞች ጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ምክንያት ዛሬ አገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረውን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በጥቂት ቻይናውያን ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
በሰራተኞች ጥቅማ ጥቅም ጥያቄ ምክንያት ዛሬ አገልግሎቱ ተቋርጦ የነበረውን የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በጥቂት ቻይናውያን ሰራተኞች ብቻ አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን አስታወቀ።
የቀላል ባቡር አገልግሎቱ ዛሬ ማለዳ ላይ ሰራተኞቹ የጥቅማ ጥቅም ጥያቄ በማንሳታቸው አገልግሎት አቋርጦ ቆይቷል።
አሁን ላይም የትራንስፖርት አገልግሎቱ እንዳይስተጓጎል በተወሰኑ ቻይናውያን ሰራተኞች አማካኝነት በ6 ባቡር አገልግሎት እየሰጠ መሆኑን ኮርፖሬሽኑ አስታውቋል።
ከቻይናውያን ሰራተኞች ውጭ ግን ኢትዮጵያውያንና ሌሎች ሰራተኞች ያቀረብነው ጥያቄ እስካልተመለሰ ድረስ ወደ ስራ አንገባም ብለዋል።
ሰራተኞቹ ከኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር ኢንጅነር ብርሃኑ በሻህ ጋር ያደረጉት ውይይት ያለ ስምምነት ተጠናቋል።
ይህን ተከትሎም ኮርፖሬሽኑ ለሰራተኞቹ የጊዜ ገደብ በማስቀመጥ ወደ ስራ የማይመለሱ ከሆነ ሌሎች በዘርፉ የሰለጠኑ ሰራተኞችን ወደ ስራ እንደሚያስገባ ገልጿል።