loading
በሱዳን የተከሰተ የጎርፍ አደጋ 10 ሰዎችን ሲገድለ ከ3 ሺህ በላይ በሚሆኑ ቤቶች ላይ ጉት አድርሷል ተባለ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ1፣ 2012 በሱዳን የተከሰተ የጎርፍ አደጋ 10 ሰዎችን ሲገድለ ከ3 ሺህ በላይ በሚሆኑ ቤቶች ላይ ጉት አድርሷል ተባለ:: አደጋው የደረሰው በደቡባዊ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ብሉ ናይል ግዛት ሲሆን በስፍራው
የሚገኝ ግድብ በመደርመሱ ውሃው አካባቢውን በማጥለቅለቁ ነው ተብሏል፡፡ አፍሪካ ንውስ እንደዘገበው በውሃ ሙላቱ ጉዳት ከደረሰባቸው ከ300 በላይ ቤቶች መካከል 1 ሺህ 800 የሚሆኑት ሙሉ በሙሉ መውደማቸው ተረጋግጧል፡፡

የጎርፍ አደጋው በ21 ትምህርት ቤቶችና በ8 መስጊዶች ላይም ከፍተኛ ጉዳት አድርሷል ነው የተባለው፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሪፖርቱ ይፋ እንዳደረገው በአደጋው ሳቢያ 50 ሺህ ሱዳናዊያን ተጠቅተዋል ብሏል፡፡

የሀገሪቱ የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ እንዳስታወቀው የግድቡ መደርመስ የጎርፍ ብቻ ሳይሆን የመሬት መንሸራተት አደጋ እያስከተለ በመሆኑ በመሰረተ ልማቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ነው፡፡ ሱዳን ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ የጎርፍ አደጋ አጋጥሟት 400 ሺህ ሰዎች የአደጋው ተጠቂዎች እንደነበሩ ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *