loading
በሲያትል የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት የተለያዩ የሕክምና ቁሳቁስ ለጤና ሚኒስቴር አስረከቡ::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 25፣ 2013 በሲያትል የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ አባላት የተለያዩ የሕክምና ቁሳቁስ ለጤና ሚኒስቴር አስረከቡ::

ስምንት አባላት ያሉት የልዑካን ቡድን ኮቪድ-19ን ለመከላከል የሚያስችሉ የሕክምና መሳሪያዎችና ሌሎች ቁሳቁስ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ፅዮን ተክሉና ለጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳሕረላ አብዱላሂ አስረክበዋል::የሲያትል ኮሚኒቲ ተወካይ አቶ ፈለቀ ወልደማርያም ድጋፉ የተደረገው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን መከላከያና ሌሎች ቁሳቁስ እንደሚገኙበት ተናግረዋል

በድጋፍ የተበረከተው ቁሳቁስ ከጤና ሚኒስቴር በተጨማሪ ለመቄዶኒያ አረጋዊያንና የአዕምሮ ሕሙማን መርጃ ለሌሎችም ግብረ ሰናይ ድርጅቶች እንደሆነም ገልፀዋልየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታዋ ወይዘሮ ፅዮን ተክሉም የኮሚኒቲው አባላት በራሳቸው ተነሳሽነት ላበረከቱት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል::

ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው በውጭ በሚገኙ ሚሲዮኖች አማካኝነት ከዲያስፖራ ማሕበረሰቡ ጋር በመወያየት በእውቀትና በገንዘባቸው ድጋፍ እንዲያደርጉ ለማስቻል እየሰራ ነው ብለዋል::

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሳሕረላ አብዱላሂ በበኩላቸው ኮቪድ-19ኝ ከመከላከል አንፃር በተለያዩ አገራት የሚኖሩ ዜጎች ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከቱ መሆኑን ገልፀዋል::

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *