loading
በሳዑዲ ዓረቢያ በእስር ላይ የነበሩ 450 ኢትጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

በሳዑዲ ዓረቢያ በእስር ላይ የነበሩ 450 ኢትጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

አርትስ 01/04/2011

አነዚህ ዜጎች የሳዑዲ አረቢያ ህግ በማይፈቅዳቸው ተግባራት ላይ ተሳትፈው በጂዛንና በተለያዩ 10 ማረሚያ ቤቶች ውስጥ በእስር የነበሩ ናቸው ብሏል የውጭ ጉዳይ ሚኒሰቴር።

ኢትጵያውያኑ አዲስ አበባ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ አለም አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ቀሪዎቹ 450 የሚሆኑት ዜጎች ደግሞ የፊታችን ታህሳስ 5 ቀን 2011 ዓመት ምህረት ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱም ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ዜጎቹ ከእስር ተፈተው ወደ እናት ሀገራቸው የገቡትም ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከሳዑዲ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት መሆኑ ነው የተገለፀው።

ከዚህ ባለፈም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በተለያዩ ሀገሮች ለእስር ተዳርገው እንዲሁም ደህንነታቸው ለአደጋ ተጋልጦ የቆየ ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገራቸው የማስመለስ ሂደቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቋል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *