loading
በስፔን ላሊጋ ባርሴሎና፣ ሪያል ማድሪድና አትሌቲኮ ማድሪድ ድል ቀንቷቸዋል

በስፔን ላሊጋ ባርሴሎና፣ ሪያል ማድሪድና አትሌቲኮ ማድሪድ ድል ቀንቷቸዋል

የስፔን ላሊጋ የ19ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትናንት እና ከትናንት በስቲያ እንዲሁም ዓርብ ተደርገዋል፡፡

ትናንት ባርሴሎና በኑካምፕ ኤይባርን አስተናግዶ በሊዮኔል ሜሲና በሊዊስ ሱዋሬዝ ሁለት ግቦች 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡ ሜሲ በላሊጋው ብቻ በ435 ጨዋታዎች 400ኛ ጎሉን አስቆጥሯል፡፡

ሪያል ማድሪድ ደግሞ ከሜዳው ውጭ ከሪያል ቤቲስ ጋር ተጫውቶ 2 ለ 1 ረትቷል፡፡ ሉካ ሞድሪች ሎስ ብላንኮስን ቀዳሚ ማድረግ ቢችልም ካናሌስ ቤቲሶችን አቻ አድርጓል፤ ሙሉ ጨዋታው ሊጠናቀቅ 2 ደቂቃዎች ሲቀሩ ዳኒ ሴባዮስ ያስቆጠራት ጎል የሳንቲ ሶላሬ ቡድን ሶስት ነጥብ እንዲያሳካ አግዛለች፡፡

አትሌቲኮ ማድሪድ በዋንዳ ሜትሮፖሊታኖ ስታዲየም በአንቱዋን ግሪዝማን የፍፁም ቅጣት ግብ ሌቫንቴን 1 ለ 0 ረትቷል፡፡

በሌሎች የሳምንቱ ጨዋታዎች አትሌቲክ ቢልባዎ ሲቪያን 2 ለ 0፣ ሌጋኘስ ሁሴካን 1 ለ 0፣ ሄታፌ ቪያሪያልን 2 ለ1 ሲረቱ ቫሌንሲያ ከሪያል ቫያዶሊድ እና ጅሮና ከ አላቬስ በተመሳሳይ በ1 ለ 1 አቻ ውጤት ተለያይተዋል፡፡

ዓርብ ዕለት ራዮ ቫይካኖ ሴልታ ቪጎን 4 ለ 2 ድል አድርጓል፡፡

ሊጉን ባርሴሎና በ43 ሲመራ አትሌቲኮ ማድሪድ በ38 ይከተላል፤ ሲቪያ እና ሪያል ማድሪድ በዕኩል 33 ነጥቦች ሶስተኛና አራተኛ ደረጃ ላይ ተገኝተዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *