loading
በሶስት ወራት ዉስጥ በአስገድዶ መደፈር በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክስ ከተመሰረተባቸዉ 40 መዝገቦች ዉስጥ 8 ዉሳኔ ማገኘታቸዉ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22፣ 2012 በሶስት ወራት ዉስጥ በአስገድዶ መደፈር በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ክስ ከተመሰረተባቸዉ 40 መዝገቦች ዉስጥ 8 ዉሳኔ ማገኘታቸዉ ተገለፀ፡፡ጠቅላይ አቃቤ ህግ ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ከመዝገቦቹ ዉስጥ በዐቃቤ ሕግ ክስ የተመሰረተባቸው የ64 ዓመቱ ተከሳሽ በአዲስ አበባ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ዕድሜያቸው ስምንት እና ዘጠኝ አመት የሆኑ ሁለት ሴት ህፃናቶችን በተለያዩ ቀናቶች ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ፈጽሞባቸዋል፡፡በዚህም ተከሳሹ የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀፅ 627(1) ተላልፎ በመገኘቱ አራት ክሶችን ተመስርቶበታል፡፡ ተከሳሽ የተከሰሰበትን ክስ ሊያስተባብል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ ተከሳሽን በአራቱም ክሶች ጥፋተኛ ነህ ብሎታል፡፡

በዚህም ሰኔ 16 ቀን 2012 ዓ.ም በዋለው ችሎት በ60 አመት እንዲቀጣ የፈረደበት ቢሆንም የተከሰሰበት ድንጋጌ ጣሪያው 25 ዓመት በመሆኑ በ 25 አመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ ውሳኔ ተሰጥቷል፡፡በተመሳሳይ ሁኔታ በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ገብርኤል ቤተ-ክርስቲያን አካባቢ ከህፃንነቷ ጀምሮ ያሳደጋትን የ15 ዓመት የእንጀራ ልጁን የደፈረው ግለሰብ በ11 ዓመት ከ9 ወር ጽኑ እስራት የተቀጡ ሲሆን ቅጣታቸዉም በቂ አይደለም ተብሎ በታመነበት ላይ የይግባኝ ክርክራችን ቀጥላል ብለዋል ጠቅላ አቃቤ ህግ።በሴቶችና ህፃናት ላይ በሚፈፀሙ ወንጀሎች ህብረተሰቡ ተጋላጭ እንዳይሆን ጥንቃቄ እንዲያደርግና ድርጊቱ ተፈፅሞ ሲያገኝም ለህግ እንዲያቀርብ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታዉቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *