loading
በቀን ኮታ የተደለደለው የነዳጅ ስርጭት

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 29 ፣ 2014 የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች በቀን መሙላት የሚችሉት የነዳጅ ኮታ ድልድል ይፋ ሆነ፡፡ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎችን ብቻ ተጠቃሚ የሚያደርገው አዲሱ የነዳጅ ድጎማ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ጀምሯል፡፡ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች የታለመለት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ ለመሆን አስፈላጊ መረጃዎችን በመስጠት በኢትዮ ቴሌኮም የሽያጭ ማዕከላት በኩል ምዝገባ
ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡


የነዳጅ ድጎማ ስርዓቱን በቴክኖሎጂ ለመደገፍ በኢትዮ ቴሌኮም በኩል መተግበሪያ በልፅጎ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ከትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚህም መሠረት በቴሌ ብር በኩል አገልግሎቱን ለማግኘት የተመዘገቡ ከ160 ሺ በላይ ተሸከርካሪዎች ከዛሬ ጀምሮ መተግበሪያውን በመጠቀም ይስተናገዳሉ፡፡


አሰራሩ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ዓመታዊ የነዳጅ ፍጆታ ተቀራራቢ የሊትር መጠን ግምት በጥናት መለየቱና እያንዳንዱ ተሽከርካሪ የሚጠቀመውን የነዳጅ መጠን ያገናዘበ ስሌት በመቀመጡ ተሽከርካሪዎቹ ያለ ብክነት የታለመ የነዳጅ ድጎማን ጥቅም ላይ እንዲያውሉ የሚያግዝ ነው፡፡ ተሽከርካሪዎቹ በቀን የተወሰነላቸው ኮታ ትንሹ ለባጃጅ 7 ሊትር ሲሆን ትልቁ መጠን ለከተማ አወቶቡስ በቀን 102 ሊትር ሆኖ ተደልድሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *