በቁጥጥር ስር የዋሉ የሜቴክ አመራርና ሰራተኞችን በተመለከተ የፌደራል ዓቃቤህግ ዛሬ መግለጫ ይሰጣል
አርትስ 03/03/2011
ባለፈው ሳምንት መጨረሻ 40 የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ አመራርና ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋሉ ሂደት እንደቀጠለም ተሰምቷል፡፡ የስራ ሃላፊዎቹና ሰራተኞቹ በቁጥጥር ስር የዋሉበት ምክንያት በይፋ አልተነገረም፡፡ ዛሬ የፌደራሉ አቃቢ ህግ በቅርቡ በሰብአዊ መብት ጥሰትና በሙስና ወንጀሎች የተጠረጠሩ እና በቁጥጥር ስር እየዋሉ በሚገኙ ከፍተኛ አመራሮች እና በሌሎች ወቅታዊ የፍትህ ጉዳዮች በተያያዘ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል፡፡