loading
በቡራዩ  ከተማ  የእሳት አደጋ በንብረ ትላይ  ጉዳት አደረሰ፡፡

በቡራዩ  ከተማ  የእሳት አደጋ በንብረ ትላይ  ጉዳት አደረሰ፡፡

በቡራዩ ከተማ ለኩ ኩሌ ቀበሌ ከሌሊቱ 8 ሰአት ከሰላሳ ላይ ኢንተማ ትሬዲንግ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር ሻማ የሚያመርት ፋብሪካ ላይ በደረሰ የእሳት አደጋ ፋብሪካው ሙሉ ለሙሉ ወድሟል፡፡

የቡራዩ  ከተማ ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር መርጊያ ሁንዴሳ ለአርትስ ቴሌቭዥን  እንደተናገሩት በእሳት አደጋው  ከፋብሪካው አቅራቢያ የሚገኙ ሁለት  ሱቆች ተቃጥለዋል፡፡

በቃጠሎ አደጋው ሳቢያ የአንድ የግለሰብ መኖሪያ ህንፃም በከፊል ጉዳት እንደደረሰበትም ኮማንደሩ አክለው ተናግረዋል፡፡

የእሳት አደጋው በኤሌክትሪክ መስመር መነካካት እንደተከሰተ ቢጠረጠርም ፖሊስ በምርመራ ሂደት ላይ እንደሆነ እና ምርመራው ሲጠናቀቅ ምክንያቱን እንደሚያሳውቅ ኮማንደር መርጊያ ነግረውናል፡፡

የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ሰራተኞች   በቦታው በመድረሳቸው አደጋው ይበልጥ እንዳይስፋፋ ሆኗል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *