loading
በቡርኪናፋሶ ምርጫ ፕሬዚዳንት ክርስቲያን ካቦሬ አብላጫ ድምፅ ማግኘት አልቻሉም ተባለ::

አዲስ አበባ፣ ህዳር 21፣ 2013 በቡርኪናፋሶ ምርጫ ፕሬዚዳንት ክርስቲያን ካቦሬ አብላጫ ድምፅ ማግኘት አልቻሉም ተባለ:: ፕሬዚዳንት ካቦሬ በምርጫው 57.87 በመቶ በሆነ ድምፅ በማግኘት ቢያሸንፉም በቂ የምክር ቤት ወንበር ባለማግኘታቸው መንግስት መመስረት አይችሉም ነው የተባለው፡፡ ፕሬዚዳንቱ የወከሉት ገዥው ፓርቲ ራሱን ችሎ መንግስት ለመመስረት ከጠቅላላው 127 የምክር ቤቱ ወንበሮች መካከል 64ቱን ማግኘት ይጠበቅበት ነበር፡፡

ይሁን እና በፕሬዚዳንት ክርስቲያን ካቦሬ የሚመራው ገዥው ፓርቲ 56 መቀመጫዎችን ብቻ ማግኘቱን ነው የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ይፋ ያደረገው፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው ካቦሬ አዲሱን ካቢኔያቸውን ለማዋቀር ከአናሳ ፓርቲዎች ጋር ጥምረት መፍጠር የግድ ይላቸዋል፡፡ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት ከሆነ ካቦሬ የወቅቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር ሆነው ከሚያገለግሉት ቪሰንት ዳቢልጉ ኒው ታይምስ ፓርቲ ጋር ጥምር እንደሚፈጥሩ ይጠበቃል፡፡

ለ27 ዓመታት በስልጣን ከቆየ በኋላ በካቦሬ ፓርቲ ከቤተ መንግስት የወጣውና በቀድሞው ፕሬዚዳንት ብላሲ ኮምፓወሬ የሚመራው ኮንግረስ ፎር ዲሞክራሲ ኤንድ ፕሮግረስ ፓርቲ 20 መቀመጫዎችን በማግኘት ሁለተኛ መሆኑ ታውቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *