loading
በቡርኪናፋሶ በተፈጸመ የታጣቂዎች ጥቃት ብዙዎች ህይወታቸዉ አለፈ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 30፣ 2013  በቡርኪናፋሶ በተፈጸመ የታጣቂዎች ጥቃት የሟች ቁጥር ከ130 በላይ መድረሱ ተሰማ  መረጋጋት በተሳነው ምእራባዊ የሀገሪቱ ክፍል የ132 ሰዎችን ህይዎት የቀጠፈውን የታጣቂዎች ጥቃት የተባበሩት መንግስታ ድርጅት በፅኑ አውግዞታል፡፡

ታጣቂቂዎች ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት ጥቃቱን ያደረሱት ዮጋ ተብላ በምትጠራው ግዛት በምትገኘውና ከኒጀር ጋር በምትዋሰነው የሶልሃን መንደር ነው፡፡
የሀገሪቱ መንግስት ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት እንዳስታወቀው ታምቡራ በተባለ አካባቢም በተመሳሳይ ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች ቆስለዋል፡፡ ይህን ተከትሎም የቡርኪናፋሶ ፕሬዚዳንት ክርስቲያን ካቦሬ መንግስት በሀገሪቲ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሄራዊ ሀዘን እንዲደረግ አዘዋል፡፡

አልጀዚራ በዘገባው እንዳስነበበው ቡርኪናፋሶ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር ከ2015 ጀምሮ ከአልቃኢዳና አይ ኤስ አይሴ ጋር ግንኙነት አላቸው በሚባሉ ቡድኖች በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ተገድለዋል፡፡ ከ1 ሚሊዮን 200 ሺህ በላይ ዜጎች ደግሞ በተደጋጋሚ ከሚደርሱ ጥቃቶች ራሳቸውን ለማዳን ሲሉ
ሀገራቸውን ጥለው ለመሰደድ ተገደዋል ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *