loading
በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ በተከሰተ የጸጥታ ችግር የ13 ሰዎች ህይወት አለፈ

በቦረና ዞን ሞያሌ ከተማ በተከሰተ የጸጥታ ችግር የ13 ሰዎች ህይወት አለፈ

አርትስ 05/04/2011

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ከሞቱት በተጨማሪ 100 የሚሆኑ ዜጎች ላይ የመቁሰል አደጋ  መድረሱን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ አስታውቋል።

የጸጥታ ችግሩ በምን እንደተቀሰቀሰ በይፋ የተገለጸ ነገር ባይኖርም በቦረና ዞን የተለያዩ አካባቢዎች የሚኖሩ ነዋሪዎች ግን መንግስት በህዝቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለማስቆም አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ የሚጠይቁ ሰልፎች  እያካሄዱ ነው፡፡

መንግስት በሁሉም አቅጣጫ እያጋጠመ ያለውን የፀጥታ ችግር ከመሰረቱ ለመቅረፍ እርምጃ እየወሰደ ነበር ያለው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ በተለያዩ አካባቢዎች የሚያጋጥሙ ችግሮችን ሙሉ በሙሉ ማስቆም ግን አዳግቶታል።

ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች አስቸኳይ ድጋፍ እንዲደረግ የክልሉ መንግስት እየሰራ መሆኑንና በአሁኑ ወቅትም ምግብ እና የተለያዩ ቁሳቁሶች የማድረስ እንቅስቃሴ መጀመሩን ቢሮው ተናግሯል።

ህዝቡ በየአካባቢው በሚያጋጥሙ ችግሮች ስሜት ውስጥ ገብቶ ራሱን ለሌላ ችግር ከማጋለጥ ይልቅ መንግስት ለሚወስዳቸው የማረጋጊያ እርምጃዎች ትብብር እንዲያደርግ  ጥሪ ተላልፏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *