loading
በቱኒዚያ የተጀመረው እስራኤልን የሚያወግዝ የተቃውሞ ሰልፍ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013  በርካታ ቱኒዚያዊያን እስራኤል በጋዛ ላይ የምትፈፅመውን ጥቃት በማውገዝ የአደባባይ ሰልፍ አካሄዱ ሰልፈኞቹ በዋና ከተማዋ ቱኒዝ ሞሃመድ 5ኛ ብሎ በሚጠራው ጎዳና ተሰባስበው ከፍልስጤም ጎን መሆናቸውን በመግለጽ እስራኤልን የሚያወግዙ መፈክሮችን ሲያሰሙ ታይተዋል፡፡ በሺዎች የሚቆጠሩት ተቃዋሚ ሰልፈኞቹ በቅርቡ በቱኒዚያና በእስራኤል መካከል የተጀመረውን መደበኛ የዲፕሎማሲ ግንኙነት ከወንጀል ትርታ በመመደብ እንዲሰርዝ ለሀገሪቱ ፓርላማ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

የቱኒዚያ ሰራተኞች ማህበራት ዋና ጸሃፊ ኑረዲን ታቡቢ በዚህ ወቅት ባደረጉት ንግግር እንደ አሜሪካና አውሮፓ ከመሳሰሉ እስራኤልን ከሚደግፉ ሀገራት የሚገቡ ሸቀጦችን ባለመግዛት ተቃውሟችንን እንግለፅ የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የእስራኤል የቅርብ አጋር የሆነችው አሜሪካ በጋዛ የተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚቀርበውን ተደጋጋሚ ጥያቄ ወደጎን ማለቷ ብዙ ትችት አስከትሏል፡፡ የፀጥታው ምክር ቤት ባለፈው ማክሰኞ ተሰብስቦ በጉዳዩ ዙሪያ ቢመክርም ያለስምምነት መበተኑ የሚታወስ ሲሆን ፈረንሳይ ከግብጽና ዮርዳኖስ ጋር በመሆን አስቸኳይ የተኩስ አቁም ስምምነት
እንዲደረግ የሚል አቋም ላይ መድረሷን ተናግራለች፡፡

ከተቀሰቀሰ ሁለተኛ ሳምንቱን በያዘው የእስራኤል-ፍልስጤም ግጭት አስካሁን በፍልስጤም በኩል 64 ህፃናትንና 38 ሴቶችን ጨምሮ ከ220 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል፡፡ እስራኤል ደግሞ ከወታደሮችም ከሲቪልም በጠቅላላው 16 ሰዎች የተገደሉባት ሲሆን ከነዚህ መካከል አንድ የአምስት ዓመት ህፃን ይገኝበታል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *