loading
በንጹሃን ሕይወትና ንብረት ላይ የሚደርስን ጥፋት አንታገስም-የአማራ ክልል::

አዲስ አበባ ፣ ሚያዝያ 20 ፣ 2014 በጎንደር ከተማ በተቀሰቀሰ ግጭት በሰው ሕይወትና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን የአማራ ክልል አስታወቀ፡፡ ግጭቱ የተቀሰቀሰው ዕለተ ማክስኞ ሲሆን ክልሉ በሰጠው መግለጫ የጸቡ ምክንያት ሃይማኖታዊ ሽፋን ያለው መሆኑን አብራርቷል፡፡ ሼህ ከማል ለጋስ የተባሉ ግለሰብ ህይወት ማለፍን ተከትሎ የቀብር ስነ ስርዓት በሚፈጸምበት ወቅት በአቅራቢያው በሚገኝ ቤተ ክርስቲያን ለቀብር የሚሆን ድንጋይ ለማንሳት የሞከሩ ሰዎችን የቤተ ክርስቲያኑ ክልል ነው አታነሱም በሚል ነው ጸቡ የተቀሰቀሰው ብሏል የክልሉ ኮሚኒኬሽን ፡፡ በዚህ መንገድ በተወሰኑ ግለሰቦች መካከል በተጀመረው ግጭት የሰው ህይወት ጠፍቷል፤ የአካል ጉዳትም ደርሷል ብሏል መግለጫው።

ተከባብሮ የመኖር ተምሳሌት በሆነችው ጎንደር ከተማ ሀይማኖትን ሽፋን ያደረገ ግጭት በመቀስቀስ የሕዝቡን አንድነት ለመስበር የተደረገው ጥረት የአማራን ህዝብ ማጥቂያ ከሆኑት ስልቶች አንዱ መሆኑንም ጠቅሷል፡፡ የአማራ ክልል መንግሥት በማንኛውንም አይነት የሰላም መደፍረስንም ሆነ በንጹሃን ሕይወት፣ አካልና ንብረት ላይ የሚደርስን ጥፋት የሚሸከምበት ጫንቃ የለውም ሲልም አሳስቧል፡፡ በጥፋተኞች ላይ ሳይውል ሳያድር አስፈላጊውን ሁሉ ህጋዊ እና ተመጣጣኝ እርምጃም የሚወሰድ
መሆኑም በመግለጫው ተመልክቷል፡፡


በመሆኑም አካባቢውን በማረጋጋት እና ህግና ሥርዓትን በማስከበር ግጭቱን በቁጥጥር ስር ለማዋል የተቻለ ሲሆን ተጠርጣሪዎችንና ሁኔታውን የሚያባብሱትን ለመያዝ ከጎንደር ከተማ ወጣቶች ጋር ውጤታማ ስሮዎች እየተሰሩ መሆኑን ከአማራ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡ የክልሉ መንግሥት በተፈጠረው ግጭት በንጹሃን ሕይወት፣ አካል እና ንብረት ላይ በደረሰው ጉዳት ጥልቅ ሀዘን የተሰማው መሆኑን በመግለጽ ለተጎጂ ቤተሰቦችም መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *