loading
በአለርት ማዕከል የሁለት ቀናት ነፃ የአይን ህክምና ሊሠጥ ነው

አርትስ 05/03/2011

ትላንት  በአለርት ሆስፒታል በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ የሆስፒታሉ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳኘው ሀገዞም እንዳስታወቁት፤ ከአልባሰር ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ጋር በጋራ በመሆን ህዳር 10 እና 11/2011 ዓ.ም .ነፃ የዓይን ምርመራ አገልግሎት እንደሚሰጥና፤ የአይን ሞራ ግርዶሽ ያለባቸውን ህሙማን በዋናነት የቀዶ ጥገና ህክምና እንደሚሰጥ ገልፀዋል፡፡
በመሆኑም በአዲስ አበባ አስሩም ክፍለ ከተሞች የአይን ጤና ችግር ያለባቸው መክፈል የማይችሉ ህሙማን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆን እንደሚችሉና በተገለፀው ቀንም የነዋሪነት መታወቂያቸውን ብቻ ይዘው መገኘት እንዳለባቸው አስረድተዋል፡፡
እንደ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ገለፃ የአልባልና ኢንተርናሽናል ፋውንዴሽን ዋና ስራ አስኪያጅ ዶክተር ያሲን ራጁ ድርጅቱ 16 የአይን ሀኪሞች፣ መነጽሮችን እና አስፈላጊ መድሃኒቶችን እና ግብአቶችን ዝግጁ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
 የአይን ጤና ችግር ያለባቸውን ህሙማን የመመርመር፣ የሞራ ችግር ያለበናቸውን የቀዶ ጥገና አገልግሎት የመስጠት እና ሌሎች የአይን ችግር የተገኘባቸውን የማማከር፣ የመድሃኒት እና የመነጽር ድጋፍ እንደሚደረግም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
 መስፈርቱም መክፈል የማይችሉ ማንኛውም የአዲስ አበባ ነዋሪ መሆን ብቻ በቂ ነው ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *