በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍጽም አረጋ የ3 ሳምንት ህጻን ልጅ በጉዲፋቻ ለማሳደግ ወሰዱ፡፡
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር አቶ ፍጽም አረጋ የ3 ሳምንት ህጻን ልጅ በጉዲፋቻ ለማሳደግ ወሰዱ፡፡
አቶ ፍጹም በፌስቡክ ገጻቸዉ ከባለቤቴ እና ከ3 ወንድ ልጆቼ ጋር በመመካከር አንዲት የ3 ሳምንት ህጻን ልጅ ለማሳደግ ዕድል ስላገኘን ትልቅ ደስታ ተሰምቶናል ብለዋል::
ላገኘነው ዕድል የአዲስ አበባ የሴቶች እና ህጻናት ቢሮን እንዲሁም የክበበ ጸሃይ ህጻናት ማሳደጊያን ከልብ እናመሰግናለን ብለዋል::
አቶ ፍጹም ልጆች ከቤተብ ጋር በፍቅር ማደግ አለባቸው እንላለን:: የምትችሉ ሁሉ ወላጅ የሌላቸውን ወላጅ ሁኑላቸው:: ውሰዱና በፍቅር አሳድጉ:: ይህንን በማድረግ አርዓያ የሆናችሁንን ሁሉ እናመሰግናለን ብለዋል::