loading
በአብዬ የሚገኘው የኢፌዲሪ መከላከያ ሰራዊት ውጤታማ የሰላም ማስከበር ሥራ ማከናወኑ ተገለፀ

አርትስ 12/02/2011
በሱዳን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ አምባሳደር የሰላም አስከባሪውን አባላት አብዬ ውስጥ አነጋግረዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ፅህፈት ቤት እንደገለፀው አምባሳደር ሽፈራው ሰራዊቱ በከፍተኛ ተነሳሽነትና በጥሩ ዲሲፕሊን ተግባሩን በማከናወኑ ምስጋና አቅርበዋል።
አያይዘውም አገራችን ለተባበሩት መንግስታት ከፍተኛ ቁጥር ያለውን የሰላም አስከባሪ ኃይል ከሚያዋጡ ጥቂት አገሮች መካከል ቀዳሚ ስፍራ ላይ የምትገኝ መሆኗን ጠቅሰዋል።

የሰላም አስከባሪው ልዩ ልዩ ክፍሎች  አምባሳደሩ በሰጡት ማብራሪያ አጠቃላይ የሰራዊቱን አደረጃጀት፣ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ፣ የአካባቢውን ሰላም ከማስጠበቅ አንጻር ያስገኘውን አበረታች ውጤት፣ ለህብረተሰቡ እያደረገያለውን ድጋፍ ፣በአካባቢው የተረጋጋ ሰላም መፈጠሩና ከቀያቸው ሸሽተው የነበሩ ነዋሪዎች ሙሉ በሙሉ መመለሳቸውን አስረድተዋል።

በተያየዘም በአብዬ የተባበሩት መንግስታት ጊዜያዊ የፀጥታ ኃይል አባላት ላበረከቱት ውጤታማ የሰላም ማስከበር ሥራ የሜዴሊያ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *