loading
በአትሌቶች የእድሜ ጉዳይ እና ዶፒንግ ላይ ትኩረት እየተደረገ አይደለም

አርትስ ስፖርት 24/02/2011

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን እያካሄደ ባለው 22ኛው መደበኛ ጉባኤ፤ የፌዴሬሽኑ ፕሬዚደንት ሻለቃ አትሌት ኃይሌ ገብረሥላሴ የተሠሩ ስራዎችን ሪፖርት አቅርቦ ጉባኤተኛው ሀሳብ ሠጥቶበታል:: አትሌቶችለውድድር በሚቀርቡበት ጊዜ የሚያስመዘግቡት ዕድሜ ተገቢ አለመሆን ፤ የተከለከሉ አበረታች መድሀኒት መጠቀም ፤ የአትሌቶች የአለም አቀፍ ውድሮች ውጤት ፤ የፓስፖርት ስርዓት አያያዝ ፤ የአትሌቶችየልምምድ ቦታዎች እና ትራክ ግንባታ ላይ በዋናነት ውይይት ተደርጎባቸዋል ። ሻለቃ ኃይሌ የዕድሜ ተገቢነት ጉዳይ ፈተና እንደሆነባቸው ጠቅሶ ፤ ከክልል አመራሮችና እና አትሌቶች ጋር በጋራ መስራት ያስፈልጋልብሏል። የዶፒንግ አቤቱታ ጉዳይም ከሌሎች ሀገራት አንፃር ሲታይ ያነሰ መሆኑን አስታውሶ ፤ ጭራሽ ለማክሰም አሁንም መስራት ያስፈልጋል ሲል አሳስቧል ። ፌዴሬሽኑንም ከገንዘብ ጥገኝነት ለማላቀቅ የተሰሩ ስራዎችይበል የሚያሰኙ ናቸው ፤ የአትሌቶች ስኬታማነትም ከፍ እያለ ነው ተብሏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *