loading
በአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ማድሪድ፣ ሙኒክ፣ ማንችስተር ሲቲና ዩናይትድ ወደ ጥሎ ማለፉ ገብተዋል

አርትስ ስፖርት 19/03/2011

የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ የምድብ አምስተኛ ጨዋታዎች ከምድብ አምስት እስከ ስምንት በሚገኙ ቡድኖች መካከል ትናንት ምሽት ተከናውነዋል፡፡

ባየርን ሙኒክ በአሊያንዝ አሬና ቤኔፊካን አስተናግዶ 5 ለ 1 ሲያሸንፍ፤ ሮበንና ሉዋንዶውስኪ ሁለት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥሩ ሪቤሪ ቀሪዋን አክሏል፡፡ አያክስ በዱሳን ታዲች ሁለት ግቦች ታግዞ ኤኢኬአቴንስን 2 ለ 0 ረትቷል፡፡ ወደ ፈረንሳይ ያቀናው ማንችስተር ሲቲ ከሊዮን ጋር በሁለት አቻ ውጤት ተለያይቷል፡፡ ኮርኔት የሊዮንን፣ ላፖርትና አጉዌሮ ደግሞ የሲቲን ግብ አስመዝግበዋል፡፡ ሻክታርዶኔስክ ሆፈንየምን 3 ለ 2 አሸንፏል፡፡

በምድብ ሰባት ሮም ላይ ሪያል ማድሪድ ባለሜዳውን ሮማን 2 ለ 0 ድል አድርጓል፤ ቤልና ቫዝኪውዝ የግቦቹ ባለቤቶች ናቸው፡፡ ሲ.ኤስ.ኬ.ኤ ሞስኮው በቪክቶሪያ ፕለዘን በ2 ለ 1 ውጤትተረትቷል፡፡ በምድብ ስምንት ደግሞ ዩቬንቱስ በማርዮ ማንዙኪች ብቸኛ ግብ ቫሌንሲያን 1 ለ 0 ድል ሲያደርግ፤ ማንችስተር ዩናይትድ ባለቀ ሰዓት በማሩዋን ፌላኒ ጎል ያንግ ቦይስን በማሸነፍጣፋጭ ድል አስመዝግቧል፡፡

በዚህም ምድብ አምስት ላይ ባየርን ሙኒክና አያክስ፣ በምድብ ስድስት ማንችስተር ሲቲ፣ በሰባተኛው ምድብ ሪያል ማድሪድና ሮማ እንዲሁም በመጨረሻው ምድብ ዩቬንቱስና ማንችስተር ዩናይትድጥሎ ማለፉን የተቀላቀሉ ቡድኖች ናቸው፡፡

ዛሬ ምሽት ከምድብ አንድ እስከ አራት የሚገኙ ቡድኖች ተጠባቂ ጨዋታቸውን ሲያደርጉ፤ ምሽት 2፡55 ላይ አትሌቲኮ ማድሪድ ከ ሞናኮ እና ሎኮሞቲቭ ሞስኮው ከ ጋላታሳራይ ሲጫወቱ ምሽት5፡00 ላይ ደግሞ ቦርሲያ ዶርትሙንድ ከ ክለብ ብሩዥ፣ ፒ.ኤስ.ቪ አይንዶቨን ከ ባርሴሎና፣ ቶተንሃም ከ ኢንተር ሚላን፣ ናፖሊ ከ ሬድ ስታር ቤልግሬድ፣ ፒ.ኤስ.ጂ ከ ሊቨርፑል እንዲሁም ፖርቶ ከሻልከ 04 ይጫወታሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *