በአዲስ አበባ ለኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሕክምና መስጫ የሚውል ፊልድ ሆስፒታል ተገነባበአዲስ አበባ ለበርካታ የኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሕክምና መስጫ የሚውል ‘አዲስ አበባ ኮቪድ-19 ፊልድ ሆስፒታል ተገነባ።
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 በአዲስ አበባ ለኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሕክምና መስጫ የሚውል ፊልድ ሆስፒታል ተገነባበአዲስ አበባ ለበርካታ የኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሕክምና መስጫ የሚውል ‘አዲስ አበባ ኮቪድ-19 ፊልድ ሆስፒታል’ ተገነባ።በቅርቡ ሥራ የሚጀምረውን ሆስፒታል የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰና የዓለም የምግብ መርኃ ግብር ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ መርቀው ከፍተውታል።በቦሌ ቡልቡላ አካባቢ የሚገኘው ይህ የፊልድ ሆስፒታል 25 ሺህ ካሬ ሜትር መሬት ላይ ያረፈ ሲሆን፥ በዓለም የምግብ መርኃ ግብር ድጋፍ የተሰራ ነው ተብሏል።
በሦስት ሣምንታት ውስጥ የተገነባው ሆስፒታሉ ቀሪ የማጠናቀቂያ ሥራዎች ተከናውነውለት ከ10 ቀናት በኋላ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚሆን ተገልጿል።ሆስፒታሉ በተለያየ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የኮሮና ቫይረስ ሕሙማን ሕክምና መስጫነት የሚውል ሲሆን በዓለም ጤና ድርጅት የጥራት ደረጃ መሰረት መገንባቱ ተጠቁሟል።ዶክተር ሊያ እንደተናገሩትም ሆስፒታሉ በዓለም የምግብ መርሃ ግብር፣ በዓለም ጤና ድርጅት እንዲሁም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ቅንጅት የተገነባነው።ለድንገተኛ ሕክምና በአጭር ጊዜ የተገነባ ቢሆንም ለረጅም ጊዜ አገልግሎት መስጠት የሚችል ማዕከል መሆኑን ገልጸዋል።
ሆስፒታሉ ቀደም ሲል ለመንግሥታቱ ድርጅት ሠራተኞች ተብሎ የተሰራ ቢሆንም ለሌሎች ሕክምና መስጫ ሆኖ እንዲያገለግልም እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።የዓለም የምግብ መርኃ ግብር ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቤስሌይ የኢትዮጵያ መንግሥት ቫይረሱን ለመከላከል ከፍተኛ ትኩረት አድርጓል ሲሉ ተናግረዋል።በተለይም የኢትዮጵያ መንግሥት ሆስፒታሉን ከተቋማቸውና ከመንግሥታቱ ድርጅት ጋር በመሆን እውን ማድረጉን አድንቀዋል።