loading
በአዲስ አበባ በደረሱ ድንገተኛ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ሕይወት አለፈ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 26 ፣ 2013  በአዲስ አበባ ከተማ በደረሱ ሁለት ድንገተኛ አደጋዎች የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአዲስ አበባ ከተማ የእሳትና አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል፡፡ የኮሚሽኑ የሕዝብ ግንኙነት ቡድን መሪ አቶ ጉልላት ጌታነህ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 አያት ጤና ጣቢያ ጀርባ ትናንት ምሽት 2 ሰዓት ከ35 ደቂቃ በግንባታ ስራ ላይ የነበረ የ35 ዓመት ወጣት በኤሌክትሪክ አደጋ መሞቱን ለኢዜአ ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ቄራ በረት አካባቢ ትናንት ከቀኑ 9 ሰዓት ከ40 አካባቢ አንድ የ50 ዓመት ግለሰብ ወንዝ ውስጥ ሞቶ ተገኝቷል።
በተጨማሪም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ጨፌ ኮንዶሚኒየም ትናንት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ገደማ አካባቢ በጣለው ከባድ ዝናብ የጎርፍ መጥለቅለቅ ተከስቷል።

ይሁንና በሰው ህይወትም ሆነ በንብረት ላይ ምንም አይነት ጉዳት ሳያደርስ መከላከል መቻሉን አቶ ጉልላት ገልጸዋል። የጎርፍ መጥለቅለቁን ለመቆጣጠር 2 ሰዓት ከ 40 ደቂቃ መፍጀቱንና ጎርፉ ወደ ሰው ቤት ገብቶ ጉዳት እንዳያደርስ የሚሄድበት የራሱ መንገድ እንዲበጅለት መደረጉንም አመልክተዋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባላትና የየአካባቢው ነዋሪዎች አደጋዎቹን ለመቆጣጠር ላደረጉት ትብብር አቶ ጉልላት ምስጋና አቅርበዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *