loading
በአዲስ አበባ አንድ ግለሰብ ስጋ አንቆት ሕይወቱ አለፈ፡፡

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 25 ፣ 2013 በአዲስ አበባ አንድ ግለሰብ ስጋ አንቆት ሕይወቱ አለፈ፡፡ በፋሲካ በአል ቀን ስጋ እየተመገበ የነበረው ወጣት ስጋው አንቆት ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል፡፡ ድንገተኛ የሞት አደጋው የደረሰው በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ካዲስኮ አካባቢ እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ገልጻል፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግኑኝነት የሚዲያ ሀላፊ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ ታደሰ ግለሰቡ ጥሬ ስጋ ገዝቶ በሚበላበት ጊዜ ነው አደጋው የደረሰበት ብለዋል፡፡ ግለሰቡ ወደ ሆስፒታል እየተወሰደ ሳለ ነው መንገድ ላይ ሂወቱ ሊያፍ የቻለው ብለውናል፡፡ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዜጎች ጥሬ ስጋ በሚመገቡበት አጋጣሚ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ሲሉ ዋና ኢንስፔክተር ማርቆስ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *