በአፋር ክልል ትናንት ምሽት 4 ሰዓት ላይ በመብረቅ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይዎት አለፈ።
አርትስ 28/12/2010
አደጋው ትናንት በፋንቲ ረሱ ጎሊና ወረዳ በጣለው ከባድ ዝናብ ወቅት በጣለው መብረቅ የደረሰ ነው።
በአደጋው ሳቢያም ሁለት ሰዎች እና 45 ፍየሎች ሞተዋል።
ፋና እንደዘገበዉ የመብረቅ አደጋው በአንድ ቀበሌ ውስጥ በሚገኙ ሁለት አካባቢዎች የደረሰ ሲሆን፥ ሟቾቹ የአንድ ቤተሰብ አባላት ናቸው።
ከዚህ ባለፈም የቤተሰቡ ንብረት የሆኑ ስድስት ፍየሎችም ሞተዋል።
ቀሪዎቹ 39 ፍየሎች ደግሞ በወረዳው በሌላ አካባቢ በጣለው መቅረብ የሞቱ ናቸዉ ተብሏል፡፡