loading
በአፍሪካ ለኮቪድ-19 ታካሚዎች ከፍተኛ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ እጥረት አለ ተባለ::

አዲስ አበባ፣የካቲት 24፣ 2013 በአፍሪካ ለኮቪድ-19 ታካሚዎች ከፍተኛ የመተንፈሻ መርጃ መሳሪያ እጥረት አለ ተባለ:: የኮሮናቫይረስ በአፍሪካ አህጉር ከተከሰተ ጀምሮ መካለኛና ዝቅተኛ ገቢ ባላቸው ሀገራት አቅምን ያገናዘበ አጋዥ የመተንፈሻ መሳሪያ እጥረት ትልቅ ፈተና መሆኑ ነው የሚነገረው፡፡
በአሁኑ ወቅት በታዳጊ ሀጋራት የሚገኙ ከ2 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በየቀኑ የኦክስጅን ድጋፍ እንደሚፈልጉ አፍሪካ ኒውስ በዘገባው አስነብቧል፡፡

የኦክስጅን እጥረት በበርካታ ሀገራት ያለ ችግር ቢሆንም በአፍሪካ ግን በከፍተኛ ደረጃ ተባብሶ መታየቱ ነው የተነገረው፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባወጣው ሪፖርት በአፍሪካ የሚገኙ የጤና ተቋማት በየትኛውም መለኪያ ሲታዩ ውስብስብ የአቅርቦት ችግር እንዳለባቸው አመላክቷል፡፡ ይህን ችግር ለመፍታት ኢንተርናሽናል ሶሊዳሪቲ የተባለ ተቋም ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመተባበር አንድ ግብረ ሃይል አቋቁሟል ነው የተባለው፡፡

አዲሱ ግብረ ሃይልም ባደረገው የዳሰሳ ጥናት ላይ ተመርኩዞ ማላዊ፣ ናይጄሪያና አፍጋኒስታንን ጨምሮ 20 ለሚጠጉ ሀገራት የኦክስጅን አቅርቦት ችግርን ለመፍታት የሚያስችል 90 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉም ተሰምቷል፡፡ በአፍሪካ በአሁኑ ጊዜ በኮሮናቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ3 ሚሊዮን 900 ሺህ በላይ የደረሰ ሲሆን ፤ ከነዚህ መካከል ከ104 ሺህ በላይ የሚሆኑት ህይዎታቸው ማለፉ ተረጋግጧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *