loading
በአፍሪካ የሳይበር ወንጀልን ለመከላከል የሚደረገው ትግል በሰብአዊ መብት ጥበቃ ላይ አደጋ እንዳይጥል ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ ተገለፀ

“ሳይበር ወንጀል” ኮምፒውተርንና ተያያዥ የመገናኛ ቴክኖሎጂዎችን ጨምሮ ከዘመናዊ የመረጃ ትስስሮች ጋር በተያያዘ የሚፈፀም ወንጀል ሲሆን ሽብርተኝነትን፣ የመረጃ ስርቆትንና ስለላን ይጨምራል። በተለይ የፋይናንሰ ተቋማት የዚህ ተግባር ዋነኛ ሰለባዎች ሆነው ይታያል።

በአዲስ አበባ ላለፉት ሶስት ቀናት ሲካሄድ የቆየውና በአፍሪካ አገራት ወንጀሉን በጋራ መከላከል በሚቻልበት መንገድ ላይ ያተኮረ ነው፡፡

በአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የመሰረተ ልማትና ኢነርጂ ዲፓርትመንት የማህበረሰብ መረጃ ክፍል ኃላፊ ሞክታር የዳሊ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለፁት ፎረሙ ለአፍሪካ የሳይበር ዘርፍ ባለሙያዎች የልምድ ልውውጥ ለማድረግ ጥሩ ዕድል ፈጥሯል።

ተሳታፊ የአፍሪካ አገሮች የሳይበር ወንጀልን ለመከላከልና በመስኩ ሊኖር የሚገባውን ደህንነት ለማጠናከር የሚያስችሉ ስልቶችን ለመቀየስ ውይይት መደረጉን ተናግረዋል።

ጉባኤው ወንጀሉን ለመከላከልና የፍትህ አካላት አቅም ለመገንባት የሚያስችሉ የዓለም አቀፍ ልምዶችና የትብብር መንገዶችም የተገኙበት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ በሳይበር ላይ ያተኮረውን የማላቦ ኮንቬንሽን ተግባራዊ ለማድረግ ሁሉም የአፍሪካ አገራት እንዲፈርሙት የማስተዋወቅና ከዘርፉ ጋር በተያያዘ ያሉ የአመለካከት ችግሮችም እንዲቀረፉ የሚያስችል ግብአቶችም የተገኘበት ነበር ብለዋል።

የሳይበር ወንጀል ለመከላከል የሚደረገው ትግል ሰብአዊ መብትን አደጋ ላይ በማይጥል መልኩ ሊከናወን እንደሚገባውም አሳስበዋል።

የአውሮፓ ህብረት ካውንስል የሳይበር ፕሮግራም ፅህፈት ቤት ፕሮጀክት ማናጄር ሜቲዮ ሉቼቲ በበኩላቸው ፎረሙ በአፍሪካውያን መካከል የሳይበር ወንጀል ለመከላከል መግባባት ላይ የተደረሰበት መሆኑ ተናግረዋል።

“የሳይበር ወንጀል ድንበር ተሻጋሪ በመሆኑ ሁሉም በጋራ ሊታገለው ይገባል፤ ፎረሙ እኛ የምናደርገውን ድጋፍ አጠናክረን እንድንቀጥል የሚያስችለንን መንገድ የጠቆመ ነው” ብለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *