በኢትዮጵያ በኮሮረና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1 መቶ 11 ደረሰ::
አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 12፣ 2012 በኢትዮጵያ በኮሮረና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1 መቶ 11 ደረሰ ::በኢትዮጵያ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸው የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ አስታዉቀዋል።ሚኒስትሯ በ24 ሰአታት ውስጥ ለ396 ሰዎች ምርመራ ተደርጎ ሶስት ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል ብለዋል።ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ ሁሉም የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ናቸው።ከዚህ ውስጥ የ11 እና የ15 አመት ታዳጊዎች ከጂቡቲ መጥተው በለይቶ ማቆያ የነበሩ ናቸው ተብሏል።አንደኛው የ18 አመት ወጣት ግን የጉዞ ታሪክ የሌለውና ቫይረሱ ከተገኘበት ሰው ጋር ንክኪ ያለው መሆኑንም ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።ይህን ተከትሎም በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 1 መቶ11 ደርሷል።ከእነዚህ ውስጥ 1 በፅኑ ህሙማን ክፍል ውስጥ ሲገኝ፥ 16 ሰዎች ደግሞ አገግመዋል ተብሏል።91 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ህክምና ላይ ይገኛሉ።