loading
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29 ደረሰ

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 24፣ 2012 በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29 ደረሰ

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ  ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ 68 የላብራቶሪ ምርመራ ተካሄዶ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት  ሰዎች መገኝታቸው ተረጋግጧል፡፡በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጡት ሶስት ግለሰቦች ሁሉም ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውም ታዉቋል፡፡የመጀመሪያዋ ታማሚ የ33 አመት ሴት ስትሆን የጉዞ ታሪኳ ጅቡቲ፣ ብራዚል፣ ህንድ እና የመጨረሻ በረራዋ ኮንጎ ብራዛቪል ነበር ተብሏል፡፡  የበሽታውን ምልክት በማሳየቷ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆና በተደረገላት የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዘች መሆኗ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡

ሁለተኛው ታማሚ የ26 ዓመት ወንድ ሲሆን የስራ ባህሪው ከተለያዩ ተጓዥ መንገደኞች ጋር ግንኙነት ያለው ሲሆን የበሽታውን ምልክት በማሳየቱ በለይቶ ማቆያ ውስጥ ሆኖ በተደረገለት የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል፡፡ሶስተኛው ታማሚ የ32 ዓመት ወንድ ሲሆን ቀደም ብሎ በበሽታው መያዙ ከተረጋገጠ ሰው ጋር ግንኙነት የነበረውና በለይቶ ማቆያ ውስጥ  ክትትል ሲደረግለት የነበረ ሲሆን በተደረገለት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙን ማረጋገጥ ተችሎል፡፡ሶስቱም ታማሚዎች በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ሲሆን ከታማሚዎቹ ጋር ግንኙነት የነበራቸውን ሌሎች ሰዎች የመለይት ስራ እየተከናወነ ይገኛል ተብሏል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በሀገራችን በለይቶ ህክምና መስጫ ማዕከል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ያሉ ሃያ አምስት  ታማሚዎች ሲኖሩ ሁለት ታማሚዎች በጽኑ ህሙማን ህክምና ክፍሌ ክትትሌ እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *