loading
በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ 100 ሰዎች ሲገኙ የ1 ሰው ህይወት አለፈ ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ 100 ሰዎች ሲገኙ የ1 ሰው ህይወት አለፈ :: ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 4950 የላቦራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ 100 ሰዎች ተገኝተዋል፡፡አዲስ የተገኙትን ጨምሮ ባጠቃላይ የኮሮና ቫይረስ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 831 ደርሷል፡፡ ትናንት ቫይረሱ የተገኘባቸው ግለሰቦች የእድሜ ክልላቸው ከ 3 እስከ 70 ዓመት ሲሆን 53 ወንዶች እና 47 ሴቶች ናቸው፡፡ከ100ው 99 ሰዎች ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 1 ሰው የብሩንዲ ዜጋ መሆኑን የገለጹት የጤና ሚኒስቴሯ ዶ/ር ሊያ ታደሰ 94 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 1 ከትግራይ ፣ 2 ከሶማሌ ፣ 3 ከኦሮሚያ ፣ እንደሆኑ ገልጸዋል፡፡ከ100ው ግለሰቦች 3ቱ የውጭ ጉዞ ታሪክ ያላቸው፣ 35ቱ በቫይረሱ ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የነበራቸው፣ 62ቱ ደግሞ የታወቀ የግንኙነት ታሪክ የሌላቸው እንደሆነ ሚኒስትሯ በሪፖርታቸው አካተዋል፡፡በተጓዳኝ ህመም ምክኒያት ህክምና ላይ የነበሩ አንድ የ70 ዓመት አዛውንት ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡በሌላ በኩል 10 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከቫይረሱ ያገገሙ ሲሆን አጠቃላይ ያገገሙት ሰዎች ቁጥርም 191 ደርሷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *