በኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ከሚቀርብባቸው መንገድ አንደኛው የሪል እስቴት ዘርፉ ነው፡፡
አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 17 ፣ 2013 በኢትዮጵያ በወንጀል ድርጊት የተገኘን ገንዘብ ወይም ንብረትን ህጋዊ አስመስሎ ከሚቀርብባቸው መንገድ አንደኛው የሪል እስቴት ዘርፉ ነው፡፡መኒ ላውንደሪንግ ወይም የገንዘብ እጥበት ሌላኛው ስሙ ነው፡፡በኢትዮጵያ ከመኒ ላውንደሪንግ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ አልሚዎች ላይ ምርመራ መጀመሩን የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለሸገር ነግሯል፡፡
ገንዘብ ከማሸሽ እና በወንጀል የተገኘን ገንዘብ ህጋዊ አስመስሎ ከማቅረብ ማዕዘን ለግዜው ስማቸውን የማንነግራችሁ የሪል እስቴት አልሚዎችን እየመረመረ መሆኑን ከጠቅላይ ዐቃ ሕግ ሰምተናል፡፡አጠቃላይ በሪል እስቴት ዘርፉ እና በሌሎችም ስራ 16 ድርጅቶች ከታክስ ስወራ ገንዘብን ከማሸሽ እና ከሌሎች የወንጀል ድርጊቶች ምክንያት ምርመራ እየተከናወነ ነው ተብሏል፡፡
አብዛኞቹ ድርጅቶችም ገንዘባቸውን ከዚህ ሀገር እንዳሸሹ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ነግሮናል፡፡በኢትዮጵያ ግዙፉ ፕሮጀክቶችን ሲያንቀሳቅሱ የነበሩ ኩባንያዎች በሀገር ቤት ያለው ሀብታቸው ባዶ ነው ገንዘቡ ውጪ ነው ያለው ተብሏል፡፡በዚህ እና በሌሎችም ከፍተኛ ብሔራዊ ወንጀል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ምርመራ ከፍቻለሁ ውጤቱንም አሳውቃለሁ ሲል ለሸገር ነግራል፡፡ (sheger fm)