loading
በኢትዮጵያ በየዓመቱ 5 ሺህ የሚደርሱ ህፃናት ከእግር መቆልመም ችግር ጋር ይወለዳሉ ተባለ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 12፣ 2014 በኢትዮጵያ በየዓመቱ 5 ሺህ የሚደርሱ ህፃናት ከእግር መቆልመም ችግር ጋር ይወለዳሉ ተባለ፡፡ ይሁን እንጂ የህክምና አገልግሎቱን ከሚፈልጉት የችግሩ ተጠቂ ህጻናት መካከል 50 በመቶዎቹ ብቻ መሆናቸውን የጤና ሚስቴር ገልጿል፡፡ በሚኒስቴሩ የህክምና አገልግሎት ዳይሬክተር ዶክተር አባስ ሀሰን ችግሩ ያለባቸውን ህጻናት በጊዜ መለየትና ፈጥኖ ማከም ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራ ለሙያተኞች መልእክት አስተላልፈዋል፡፡


የጤና ተቋማት የተሻለ አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ጥረት እየተደረገ ነው ያሉት ዳይሬክተሩ ሙያተኞችን የማሰልጠንና በችግሩ ዙርያ በየደረጃው ላሉ አመራሮችን ግንዛቤ የማሳደግ ስራ በስፋት መሰራት እንዳለበትም ጠቁመዋል፡፡ በእግር መዞር ምክንያት የሚፈጠርን የአካል ጉዳተኝነት ለመቀነስ ርብርብ እንዲደረግ በማሳሰብ
ባለድርሻ አካላት ችግር ያለባቸው ህጻናትን ወደ ህክምና የማድረስ ሃፊነታቸውን እንዲወጡ ጠይቀዋል፡፡ ይህንን ችግር በመቅረፍና ህጻናትን ከአካል ጉዳተኝነት በማላቀቅ ጤናማ ዜጋ ማድረግ የሚቻልበት ስራ መጠናከር እንደሚገባውም ጥሪ ቀርቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *