
በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ዉስጥ በኮቪድ 19 ምክንያት ሞት አልተመዘገበም::
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24፣ 2013 በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ዉስጥ በኮቪድ 19 ምክንያት ሞት አልተመዘገበም:: በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በኮቪድ -19 ምክንያት የሞት መጠን አልተመዘገበም ተባለ፡፡ የጤና ሚኒስቴር የ24 ሰዓትን ሪፖርት ባወጣዉ መረጃ ኢትዮጵያ ዉስጥ ከረጅም ግዜ በኋላ በኮቪድ- 19 ምክንያት ሞት ያልተመዘገበበት ቀን ሆኗዋል፡፡ በ24 ሰዓቱ በተደረገ 4 ሺህ 974 የላብራቶሪ ምርመራ 137 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በጽኑ የታመሙ 145 ሰዎች ሲሆኑ ከበሽታዉ ያገገሙ 70 ናቸዉ::ኮቪድ 19 ክትባት በኢትዮጵያ መሰጠት ከተጀመር ወዲህ ከ2 ሚለዮን 19 ሺህ በላይ ሰዎች ክትባት አግኝተዋል፡፡