በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ መምርመራ 14 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 11፣ 2012 በኢትዮጵያ በ24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ የላቦራቶሪ መምርመራ 14 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸው
የጤና ሚኒስቴር በመግለጫው እንዳስታወቀው በ24 ሰዓታት ውስጥ በ3 ሺህ 271 ሰዎች ላይ በተደረገ ምርመራ ነው ታማሚዎቹ የተለዩት፡፡
በቫይረሱ የተያዙት ሁሉም ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ እድሜያቸው ከ9 እስከ 65 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ 11 ወንዶችና 3 ሴቶች መሆናቸው ታውቋል፡፡
በምርመራ በሽታው እንዳለባቸው ከታወቁት 14 ሰዎች መካከል ዘጠኙ ከአዲስ አበባ፣ አንድ ከትግራይ ሶስት ከሶማሌ እና አንድ ከኦሮሚያ ክልሎች ናቸው ተብሏል፡፡
ከነዚህም መካከል ስድስቱ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና ሰባቱ በሽታው ካለባቸው ሰዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው፣ አንድ ሰው ደግሞ የጉዞ ታሪክም ሆነ በሽታው ካለባቸው ሰዎች ጋር ንክኪ የሌለው እንደሆነ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡
በአሁኑ ነጊዜ በሀገራችን በቫይረሱ የተያዙት ሰዎች ቁጥር 365 የደረሰ ሲሆን ከበሽታው ያገገሙት ደግሞ 120 ደርሰዋል