loading
በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ምርመራ 1 መቶ 42 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸዉ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2012 በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ ምርመራ 1 መቶ 42 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኘባቸዉ፡፡
የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳስታወቁት ባለፉት 24 ሰዓታት ዉስጥ በተደረገዉ የ4 ሺህ 1መቶ 20 የላብራቶሪ ምርመራ 1 መቶ 42 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸዉ ሰዎች ቁጥር 1 ሺህ 4 መቶ 86 ደርሷል፡፡ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸዉ 84 ወንድ እና 57 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸዉም ከ7 አስከ 78 ዓመት ዉስጥ ይገኛል፡፡በዜግነት 140 ዉ ኢትዮጵያዊያን ሲሆኑ ሁለቱ የፖርቹጋልና የጅቡቲ ዜጎች ናቸዉ፡፡ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸዉ 1 መቶ 26ቱ ሰዎች ከአዲስ አበባ ፤ሁለቱ ከአፋርክልል፤ሰባት ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፤ ስድስት ሰዎች ከአማራ ክልል እና አንድ ሰዉ ከሶማሌ ክልል ናቸዉ፡፡የጤና ሚኒስትርዋ በእለታዊዉ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መረጃቸዉ ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ የሶስት ኢትዮጵያዉያን ህይወት ማለፉን ገልጸዋል፡፡የመጀመርያዋ ህይወታቸዉ ያለፈዉ የ71 ዓመት ሴት የአዲስ አበባ ነዋሪ ሁለተኛ የ46 ዓመት ወንድ የኦሮሚያ ክልለ ነዋሪ ፤ ሶስተኛ ደግሞ የ40 ዓመት ወንድ የደቡብ ክልል ነዋሪ ናቸዉ፡፡የመጀመርያዋ ግለስብ በሆስፒታል ዉስጥ ህክምና ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸዉ ታዉቋል፡፡ሁለቱ ህይወታቸዉ አልፎ ለአስክሬን ምርመራ በሆስፒታል በተደረገ ምርመራ የኮሮና ቫይረስ እንደተገኘባቸዉ ታዉቋል፡፡ባጠቃለይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸዉና ህይወታቸዉ ያለፈ ሰዎች ቁጥር አስራ ሰባት ደርሷል፡፡በሌላ በኩል በትላንትናዉ እለት አስራ አምስት ሰዎች ከኮሮና ቫይረስ ያገገሙ ሲሆን አስካሁንም በሀገራችን ከበሽታዉ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 2 መቶ 46 ደርሷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *