loading
በኢትዮጵያ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችንና ድንገተኛ ጉዳቶችን የመከላከልና የማከም ስራ ላይ ክፍተት መኖሩን አንድ ጥናት አረጋገጠ።

አርትስ 19/03/2011

ጥናቱን የሰራው ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችና ድንገተኛ ጉዳቶች ኮሚሽን ሲሆን  ከጤና ሚኒስቴርና ከባለድርሻ አካላት ጋር በጉዳዩ ላይ ውይይት ባካሄደበት ወቅት ይፋ አድርጎታል።

የኮሚሽኑ ሊቀ መንበር ፕሮፌሰር አብርሃም ኃይለመልዓክ እንደገለጹት በኢትዮጵያ ከሚከሰት የሞት መጠን ከ50 በመቶ በላይ የሆነው ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችንና ድንገተኛጉዳቶችን መከላከልና ማከም ላይ ባለ ክፍተት የሚከሰት ነው።

የኮሚሽኑ ፀሐፊ ዶክተር ውብአየ ዋለልኝ በበኩላቸው እንዳሉት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችና ድንገተኛ ጉዳቶች የተሰጣቸው ትኩረት አነስተኛ በመሆኑ በኀብረተሰቡ ላይ ማህበራዊናኢኮኖሚያዊ ጫና እያደረሱ ይገኛሉ ።

የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ዶክተር ሊያ ታደሰ እንዳሉት ሚኒስቴሩ ከዚህ በኋላ  ከኮሚሽኑ ያገኘውን ጥናት እንደ ግብዓት በመጠቀም እየተስፋፋ በመጣው ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችናድንገተኛ ጉዳቶችን መከላከልና ማከም ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይሰራል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *