በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ህይወታቸውን ላጡ የ 40 ቀን መታሰቢያ ተደረገ
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ህይወታቸውን ላጡ የ 40 ቀን መታሰቢያ ተደረገ
ከአዲስ አበባ ወደ ናይሮቢ ለመጓዝ ከቦሌ አለም አቀፍ አይሮፕላን ጣቢያ በበረራ ቁጥር ኢቲ 302 እንደተነሳ በስድስት ደቂቃ ውስጥ በወደቀው ቦይንግ 737 ማክስ ኤይት አደጋ ህይወታቸው ላጡ መንገደኞች እና ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኞች የ40 ቀን መታሰቢያ ትላንት ተደርጎላቸዋል፡፡
የ40 ቀን መታሰቢያ ስነሰርዓቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦይንግ 737 ማክስ 8 አውሮፕላን በተከሰከሰበት ስፍራ በደብረዘይትና አቅራቢያ ኤጀሬ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ታሰቦ ውሏል፡፡
የቢሾፍቱ ከተማና አካባቢ ነዋሪዎች የ 40 ቀን መታሰቢያዉን ማዘጋጀታቸውን ሰምተናል፡፡
በመታሰቢያዉ በአደጋዉ ህይወታቸዉን ያጡ ቤተሰቦች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል፡፡የ መታሰቢያ የፀሎት ስነስርዓት ተደርጎላቸዎል፡፡
ዘገባዉ የአቢ ፍቃዱ ነዉ፡፡