በኢትዮጵያ ከ8 ሚሊዮን በላይ ህፃናት ለከፍተኛ የጉልበት ብዝበዛ ተጋላጭ አንደሆኑ ተነገረ፡፡
ይህ የተነገረው የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር በህፃናት ጉልበት ብዝበዛ ዙሪያ በአዲስ አበባ ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ባደረገው ውይይት ነው፡፡
በውይይቱ በኢትዮጲያ እድሜያቸው ከ 5 እሰከ 17 ዓመት ከሆኑ ሕፃናት ውስጥ 8.7 ሚሊዮኑ በተለያዩ የሃገሪቱ ከተሞች እና ገጠራማ አካባቢዎች ለጉልበት ብዝበዛ የሚያጋልጡ ስራዎቸ ይሰራሉ ተብሏል፡፡
በኢትዮጲያ የህፃናት ጉልበት ብዝበዛን በሚመለከት ሕጎች የተቀመጡ ቢሆንም ተግባራዊነታቸው ላይ ያለው ክፍተት በተፈለገው ደረጃ ህፃናቱን ለመታደግ እና ቁጥሩን ለመቀነስ እንዳይቻል አድርጓል ፡፡