በኢትዮጵያ ወጣቶች ለኮሮና ቫይረስ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸዉን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮትአስታወቀ፡፡
በኢትዮጵያ ወጣቶች ለኮሮና ቫይረስ ይበልጥ ተጋላጭ መሆናቸዉን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮትአስታወቀ፡፡
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 5፣ 2012 ኢንስቲትዩቱ እንዳስታወቀዉ በኢትዮጵያ አስከ ማክሰኞ ዕለት በኮሮና ቫይረስ ከተያዙ 261 ሰዎች መካከል 91 የሚሆኑት እድሜያቸዉ ከ15- 24 ዓመት መሆኑን የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዮት ያወጣዉ አህዛዊ መረጃ ይጠቁማል፡፡ከ25 -34 ባሉት የእድሜ ክልል ዉስጥ ያሉት ደግሞ በሁለተኛ ደረጃ ተጋላጭ መሆናቸዉን ነዉ መረጃዉ ያመላከተዉ ፡፡ከተያዙት ሰዎች መካከል 43 የሚሆኑት ዕድሜያቸዉ ከ35-44 ዓመት የሆኑት ሲሆኑ 26 ሰዎች ደግሞ ዕድሜያቸው ከ45-59 ዓመት እንደሆነ ተመልክቷል።ከ60 ዓመት በላይ የሆኑ 18 ሰዎች ብቻ ቫይረሱ የተገኘባቸው መሆኑን የጠቆመው መረጃው፣ በተመሳሳይ ዕድሜያቸው ከ5-14 የሆኑ ሰባት ልጆች እና ዕድሜው ከአምስት ዓመት በታች የሆነ አንድ ሕፃን ብቻ ለኮሮናቫይረስ ተጋላጭ ሆነው መገኘታቸውን አመልክቷል።